ሮሜ 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንግዲህ ምን ልበል፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? በጭራሽ! እኔ ደግሞ ከብንያም ወገን፥ ከአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 እስቲ ደግሞ ልጠይቅ፦ እግዚአብሔር የራሱን ሕዝብ ጥሎአልን? ከቶ አልጣለውም! እኔም ራሴ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከአብርሃም ዘር የሆንኩ የብንያም ነገድ ነኝ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 እንግዲህ እላለሁ፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? አይደለም፤ እኔ ደግሞ ከአብርሃም ዘር ከብንያም ወገን የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 እንግዲህ፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን? እላለሁ። አይደለም እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና። See the chapter |