Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሮሜ 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ይህም እርስ በእርሳችን በእናንተና በእኔ ዘንድ ባለች እምነት፥ አብረን እንድንጽናና ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ይኸውም እናንተና እኔ በእያንዳንዳችን እምነት እርስ በርሳችን እንድንበረታታ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ይህንንም ማለቴ እኔ በእናንተ እምነት፥ እናንተም በእኔ እምነት እርስ በእርሳችን እንድንጽናና ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ይህ​ንም ማለቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ባለች በእ​ና​ን​ተና በእኔ እም​ነት አብ​ረን በእ​ና​ንተ እን​ድ​ን​ጽ​ናና ነው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።

See the chapter Copy




ሮሜ 1:12
17 Cross References  

የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር አቻ የሆነ ክቡር እምነትን ላገኙ፤


የጋራ በሆነው እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆንከው ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከአዳኛችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ሰላም ይሁን።


ስለዚህ ተጽናንተናል፤ ክመጽናናታችንም ሌላ ስለ ቲቶ ደስታ እጅግ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ልቡ በሁላችሁም እረፍት አግኝቷል።


በእግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ወደ እናንተ መጥቼ ከእናንተ ጋር እንዳርፍ ነው።


እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ጸጋ ባየ ጊዜ ደስ አለው፤ ሁሉንም በልባቸው ፈቃድ በጌታ ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው፤


ወዳጆች ሆይ! ስለ ጋራ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅዱሳን ሁሉ ስለ ተሰጠው እምነት እንድትጋደሉ እንድመክራችሁና እንድጽፍላችሁ ግድ ሆነብኝ።


ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአባት እንደተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት የሚመላለሱ ሆነው በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።


በደስታ እንድሞላ እንባህን እያስታወስኩ ላይህ እናፍቃለሁ።


አንድ ጌታ፥ አንድ እምነት፥ አንድ ጥምቀት፤


ወደ ስፔን በምሄድበት ጊዜ፥ ከእናንተ ጋር ተደስቼ ጥቂት ካሳላፍሁ በኋላ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ሳልፍ ላያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።


የሚያጸናችሁን መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁ፤


ወንድሞች ሆይ! በሌሎቹ ሕዝቦች እንዳገኘሁት በእናንተም ፍሬ ለማግኘት ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ልመጣ እንዳቀድሁ እስከ አሁን ግን እንደ ተከለከልሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements