Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ራእይ 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም ለአምስት ወር ያህል የመጉዳት ሥልጣን አላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንደ ጊንጥም ያለ፣ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ ደግሞም ሰዎችን ዐምስት ወር የሚያሠቃዩበት ኀይል በጅራታቸው ላይ ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንደ ጊንጥ ጅራትና መንደፊያ ነበራቸው፤ በጅራታቸው ውስጥ ሰዎችን ለአምስት ወር የሚጐዱበት ኀይል ነበራቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው፤ በጅራታቸውም መውጊያ አለ፤ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እንደ ጊንጥም ጅራት ያለ ጅራት አላቸው በጅራታቸውም መውጊያ አለ፥ ሰዎችንም አምስት ወር እንዲጐዱ ሥልጣን አላቸው።

See the chapter Copy




ራእይ 9:10
7 Cross References  

ለአምስትም ወር እንዲያሰቃዩአቸው እንጂ እንዲገድሉአቸው አልተፈቀደላቸውም፤ እነርሱም የሚያደርሱት ሥቃይ ጊንጥ ሰውን ሲነድፍ እንደሚያደርሰው ስቃይ ዓይነት ነው።


ከጢሱም አንበጣዎች ወደ ምድር ወጡ፤ የምድርም ጊንጦች እንዳላቸው ሥልጣን ዓይነት ሥልጣን ተሰጣቸው።


የፈረሶቹ ሥልጣን በአፋቸውና በጅራታቸው ነውና፥ ጅራታቸው እባብን ይመስላል፤ ራስም አላቸው፤ በእርሱም ጉዳትን ያደርሳሉ።


አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችሁ ነበር፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ።’ ”


“አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ ነበር፥ እኔ ግን እጨምርበታለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችሁ ነበር፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” ብሎ እንደ ብላቴኖቹ ምክር ተናገራቸው።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ ኩርንችትና እሾህ ከአንተ ጋር ቢኖሩም፥ በጊንጦች መካከል ብትቀመጥም፥ አትፍራ፥ ቃላቸውንም አትፍራ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና ቃላቸውን አትፍራ፥ ፊታቸውንም አትፍራው።


ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements