Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ራእይ 6:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ጸንቶ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ታላቁ የቍጣቸው ቀን መጥቷልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሏቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ታላቁ የቊጣ ቀን መጥቶአል፤ ማን ሊቋቋመው ይችላል?” አሉአቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፤ ማንስ ሊቆም ይችላል?” አሉአቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው።

See the chapter Copy




ራእይ 6:17
20 Cross References  

እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳትና እንደ አጣቢ ሳሙና ነውና፤ የሚመጣበትን ቀን መቋቋም የሚችል ማን ነው? እርሱስ ሲገለጥ የሚቆም ማን ነው?


ጌታም በሠራዊቱ ፊት ድምፁን ያሰማል፥ ሠራዊቱ እጅግ ብዙ ነውና፥ ቃሉንም የሚፈጽም እርሱ ኃያል ነውና፥ የጌታ ቀን ታላቅና እጅግ የሚያስፈራ ነውና ማንስ ይችለዋል?


የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ፈረሶች አንቀላፉ።


የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ ምልክት እያደረጉ፥ በታላቁና ሁሉን በሚገዛው በእግዚአብሔር ቀን ለሚሆነው ጦርነት እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


ታላቁና የሚያስፈራው የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣል።


ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፥ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


አሕዛብም ተቈጡ፤ ቁጣህም መጣ፤ በሙታንም የምትፈርድበት ዘመን መጣ፤ ለባርያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን፥ ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን የምትሰጥበት ምድርንም የሚያጠፉትን የምታጠፋበት ዘመን መጣ።”


የመጀመሪያ ቦታቸውን ያልጠበቁትን ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘለዓለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ከጨለማ በታች ጠብቆአቸዋል።


እንግዲህ ሊመጣ ካለው ከዚህ ሁሉ ለማምለጥ፥ በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትችሉ እየጸለያችሁ ሁልጊዜ ትጉ።”


የቤትሼሜሽም ሰዎች፥ “ታዲያ በዚህ ቅዱስ አምላክ በጌታ ፊት ማን መቆም ይችላል? ታቦቱስ ከዚህ ወጥቶ ወደ ማን ይሂድ?” አሉ።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ጌታ በቀኝህ፥ ነገሥታትን በቁጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።


የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።


የጌታ ቀን ቀርቧልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል ከአምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል።


የጌታ ቀን መጥቷልና፥ እርሱም ቀርቧልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፥ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ።


በቁጣው ፊት ማን ይቆማል? የቁጣውንስ ንዳድ ማን ይቋቋማል? መዓቱ እንደ እሳት ፈሰሰ፤ ከእርሱ የተነሣ ዓለቶች ተሰነጣጠቁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements