Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ራእይ 12:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እርሷም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ልትወልድም ምጥ ይዟት ተጨንቃ ትጮኻለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እርሷም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት ተጨንቃ ጮኸች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እርስዋም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ልትወልድም ምጥ ይዞአት ተጨንቃ ትጮኽ ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፤ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።

See the chapter Copy




ራእይ 12:2
12 Cross References  

በጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ከዚያም ዘንዶው ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ሕፃንዋን ለመዋጥ ልትወልድ በተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።


ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ እስኪቀረጽ ድረስ ስለ እናንተ እንደገና ምጥ ይዞኛል።


ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና በደስታዋ ምክንያት መከራዋን ከቶውን አታስበውም።


“አንቺ የማትወልጅ መካን! ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ! እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና” ተብሎ ተጽፎአልና።


እርሱም ይቆማል፥ በጌታ ኃይል፥ በግርማዊው በጌታ በአምላኩ ስም መንጋውን ያሰማራል፤ እነርሱም ተደላድለው ይኖራሉ፤ አሁን እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ታላቅ ይሆናልና።


ከነፍሱ ሥቃይ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ አገልጋዬ በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፤ ኃጢአታቸውንም ይሸከማል።


አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።


የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ ጌታ፥ በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።


የጩኸት ድምፅ ከከተማ፥ ድምፅም ከመቅደስ፥ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የጌታ ድምፅ ተሰምቶአል።


አሁንስ ለምን ጮክ ብልሽ ታለቅሻለሽ? በአንቺ ዘንድ ንጉሥ ስለ ሌለ ነውን? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የያዘሽ፥ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን?


እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements