Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 99:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ፍትሕን የምትወድ ኀያል ንጉሥ ሆይ! ቅንነትን መሥርተሃል፤ በእስራኤል ዘንድ ፍትሕንና ጽድቅን ተግባራዊ አድርገሃል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥

See the chapter Copy




መዝሙር 99:4
17 Cross References  

ጌታ ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፥ ቅን ሰው ፊቱን ያየዋል።


በልብሱና በጭኑም ላይ “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም ተጽፎአል።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።


ሁሉን የሚችል አምላክን እናገኝ ዘንድ አንችልም፥ በኃይል ታላቅ ነው፥ በፍርድና በጽድቅም ሃብታም ነው፤ አይጨቁንምም።


ወላጁን ላጣና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ ስደተኛውንም ስለሚወድ ምግብና ልብስ ይሰጠዋል።


ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።


ይህም በሁሉ ላይ ለመፍረድ ነው፤ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኀጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዐመፀኞችም ኀጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ”


ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፥ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፥ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።


በምድርም ፍርድን እስኪያደርግ ድረስ ያበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።


ዓለምንም በጽድቅ አሕዛብንም በቅንነት ይፈርዳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements