Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 83:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኗቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በምድያም ላይ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤ በቂሶንም ወንዝ በሲሣራና በኢያቢስ ላይ ያደረስኸው ይድረስባቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በምድያማውያን፥ በሲሣራና በያቢንም ላይ በቂሾን ወንዝ ያደረግኸውን በእነዚህም ላይ አድርግ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አቤቱ፥ መታ​መ​ኔን እይ​ልኝ፥ ወደ ቀባ​ኸ​ውም ፊት ተመ​ል​ከት።

See the chapter Copy




መዝሙር 83:9
9 Cross References  

የጦረኞች ጫማ ሁሉ፤ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፤ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም።


ከዱሮ ጀምሮ የታወቀ ያ የቂሶን ወንዝ፥ የቂሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰዳቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በኃይል እርገጪ።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድያምን በሔሬብ ዐለት አካባቢ እንደ መታ፤ በጅራፍ ይገርፋቸዋል፤ በግብጽ እንዳደረገውም ሁሉ፤ በትሩን በውሆች ላይ ያነሣል።


እኔም የኢያቢስን ሠራዊት አዛዥ ሲሣራን ከሠረገሎቹና ከሠራዊቱ ጋር ቂሶን ወንዝ እንዲመጣ አነሣሣዋለሁ፤ በእጅህም አሳልፌ እሰጥሃለሁ።’”


ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሞዓብ ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የሞዓባውያን አባት ነው።


ታናሺቱም ደግሞ ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም፦ የወገኔ ልጅ ስትል አሞን ብላ ጠራችው፥ እርሱም እስከ ዛሬ የአሞናውያን አባት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements