Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 68:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 በምሥራቅ በኩል በሰማየ ሰማያት ላይ ተቀምጦ ለሚጓዘው የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ግርማው በእስራኤል ላይ፣ ኀይሉም ከደመናት በላይ ነው፣ እግዚአብሔርን ብርታት የአንተ ነው በሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ግርማው በእስራኤል ላይ፥ ኀይሉም በሰማይ ላይ ስለ ሆነ የአምላክን ኀይል ዐውጁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ሰማ​ይና ምድር፥ ባሕ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

See the chapter Copy




መዝሙር 68:34
9 Cross References  

የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።


ከግርማዊው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው!” የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ገናናነትን ተቀብሏል።


ሃሌ ሉያ። ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥ በኃይሉ ጠፈር አወድሱት።


“ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ ጌታ ያለ ማንም የለም።


መኖሪያህ የዘለዓለም አምላክ ነው፥ የዘለዓለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፥ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦ አጥፋው ይላል።


የጌታ ድምፅ በኃይል ነው፥ የጌታ ድምፅ በታላቅ ክብር የተሞላ ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements