Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 66:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፥ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ባሕሩን የብስ አደረገው፤ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ ኑ፣ በርሱ ደስ ይበለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እርሱ ባሕሩን ወደ ደረቅ መሬት ለውጦአል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ወንዙን በእግር ተሻግረዋል፤ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።

See the chapter Copy




መዝሙር 66:6
13 Cross References  

ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ።


ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፥ ውኆችን እንደ ግንብ አቆመ።


እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።


የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተራመዱ፤ ውኆችም በቀኛቸውና በግራቸው ግድግዳ ሆኑላችው።


እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት በሚሻገሩ ጊዜ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳንስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።


ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ላይ ተሻገረ፤’


Follow us:

Advertisements


Advertisements