Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 45:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ፤ ከንፈሮችህም የጸጋ ቃል ያፈልቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ የተዋብክ ነህ፤ ንግግርህም ሞገስ የሞላበት ነው፤ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ባርኮሃል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ስለ​ዚህ ምድር ብት​ነ​ዋ​ወጥ፥ ተራ​ሮ​ችም ወደ ባሕር ልብ ቢፈ​ልሱ አን​ፈ​ራም።

See the chapter Copy




መዝሙር 45:2
19 Cross References  

ሁሉም ይመሰክሩለት ነበር፤ ከአፉም ከሚወጡት ቃላት ጸጋ የተነሣ እየተደነቁ፦ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።


እንዲህ ያለው ቅዱስ፥ ነቀፋ የሌለበት፥ ንጹሕ፥ ከኃጢአተኞች የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ ሊቀ ካህናት ሊኖረን ይገባል፤


ዘቦቹም “እንደዚህ ሰው ማንም ከቶ አልተናገረም፤” ብለው መለሱ።


በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፥ ሞገስንና ግርማን በላዩ አኖርህ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


የልብን ንጽሕናን የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፥ ንጉሥ ወዳጁ ይሆናል።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


በጎነቱ በውበቱም እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጎልማሶችን፥ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅቱን ያሳምራል።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ ጌታ ቀብቶኛልና፥ ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።


ጥንቃቄን ትጠብቅ ዘንድ ከንፈሮችህም እውቀትን እንዲጠብቁ።


ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ይመለከታሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements