Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 37:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰይፋቸው የገዛ ልባቸውን ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ነገር ግን ሰይፋቸው የራሳቸውን ልብ ይወጋል፤ ቀስታቸውም ይሰበራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ አንተ ስማኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 37:15
18 Cross References  

ያላወቁት ወጥመድ ይምጣባቸው፥ የሸሸጉትም ወጥመድ ይያዛቸው፥ በዚህ ወጥመድ ውስጥ ይውደቁ።


በዚያም ቀን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት እሰብራለሁ።”


አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፥ ኃያላኖችዋ ተያዙ፥ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ ጌታ ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፥ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።


የጌታን ሥራ፥ በምድር ያደረገውንም ተኣምራት እንድታዩ ኑ።


አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።


“በዚያ ቀን፦ ‘ባሌ’ ብለሽ ትጠሪኛለሽ እንጂ ዳግመኛ፦ ‘በኣሌ’ ብለሽ አትጠሪኝም፥ ይላል ጌታ፤


በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፈንታ ነገሠ።


ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ “እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች መጥተው እንዳይወጉኝ፥ እንዳያዋርዱኝም፥ አንተው ሰይፍህን መዘህ ውጋኝ” አለው። ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለ ነበር፥ እምቢ አለው። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት።


የኀያላን ቀስቶች ተሰበሩ፤ ደካሞች ግን በብርታት ታጥቀዋል።


የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።


ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።


እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ጦርነትን ያስቆማል፥ ቀስትን ይሰብራል፥ ጦርንም ይቆራርጣል፥ በእሳትም ጋሻን ያቃጥላል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements