Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 37:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፤ በታላቅ ሰላምም ሐሤት ያደርጋሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ትሑቶች ምድርን ይወርሳሉ፤ ብልጽግናንና ሰላምን በማግኘት ይደሰታሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ወዳ​ጆቼም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼም ባላ​ጋራ ሆኑኝ፥ ከበ​ውም ደበ​ደ​ቡኝ፥ ዘመ​ዶቼም ተስፋ ቈር​ጠው ተለ​ዩኝ።

See the chapter Copy




መዝሙር 37:11
16 Cross References  

የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።


በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ።


ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ማን ነው? በመልካም አኗኗር ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።


ሕግህን ለሚወድዱ ብዙ ሰላም ነው፥ ዕንቅፋትም የለባቸውም።


ከሰውም ማስተዋል ሁሉ በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።


ትእዛዜን ብትሰማ ኖሮ፥ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ፤ ጽድቅን፥ እግዚአብሔርን መምሰልን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ መጽናትን፥ የዋህነትን ግን ተከተል።


ስለዚህ ርኩሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።


በዘመኑም ጽድቅ ያብብ፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ይብዛ።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን እንዴት አበዛህ! የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።


ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይታወክ፤ አይፍራም።


በሕይወት እንድትኖሩ፥ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ጌታ አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።


ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።


ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል፤ ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፥ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements