Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 36:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ኃጢአተኛ በራሱ የሚያስት ነገርን ይናገራል፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዐይኖቹ ፊት የለም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እንደ ሣር ፈጥ​ነው ይደ​ር​ቃ​ሉና፥ እንደ ለመ​ለመ ቅጠ​ልም ፈጥ​ነው ይረ​ግ​ፋ​ሉና።

See the chapter Copy




መዝሙር 36:2
15 Cross References  

እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን መሐላ ቃል በሚሰማበት ጊዜ፥ በልቡ ራሱን በመባረክ፥ ‘ምንም እንኳ እንደ ልቤ ደንዳናነት ብሄድ ሰላም አለኝ’ ብሎ ያስባል። ይህም በለምለሙም ሆነ በደረቁ መሬት ላይ ጥፋትን ያመጣል።


በሞተ ጊዜ ከእርሱ ጋር ምንም አይወስድምና፥ ክብሩም ከእርሱ በኋላ አይወርድምና።


ክፉ በነፍሱ ፈቃድ ይኮራልና፥ ስግብግብም ይረግማል፥ ጌታንም ይንቃል።


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


ስለዚህ ምን ይሁን? እኛ እንበልጣለንን? በጭራሽ! አይሁዳውያንንም ግሪካውያንንም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደ ሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋል፤


እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን፦ “ባልንጀራዬስ ማን ነው?” አለው።


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል?


አንቺስ፦ ‘ራሴን አላረከስኩም በዓሊምንም አልተከተልኩም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ያለውን መንገድሽን ተመልከቺ፥ ምን እንዳደረግሽም እወቂ፤ በመንገዶችዋ ላይ ወድያና ወዲህ የምትቅበዘበዥ ወጣት ግመል ሆነሻል፤


የእግዚአብሔርን ጽድቅ ባለማወቅ፥ የራሳቸውንም ጽድቅ ለመመሥረት በመፈለግ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም።


ንጉሡም ሆነ እነዚህን ቃላት ሁሉ የሰሙ ባርያዎቹ በጠቅላላ አልፈሩም ልብሳቸውንም አልቀደዱም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements