Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን ታደርጋቸዋለህ፥ ጌታ በቁጣው ይውጣቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዘራቸውን ከምድር፣ ዘር ማንዘራቸውንም ከሰው ልጆች መካከል ታጠፋለህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ትውልዳቸውን ከምድር ላይ ታጠፋለህ፤ ዘራቸውንም ከሕዝቦች መካከል ለይተህ ትደመስሳለህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከማ​ኅ​ፀን ጀምሮ በአ​ንተ ላይ ተጣ​ልሁ፤ ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ጀም​ረህ አንተ አም​ላኬ ነህ።

See the chapter Copy




መዝሙር 21:10
8 Cross References  

ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


ይህም ኃጢአቱ ለሥረወ መንግሥቱ መጥፋትና በሙሉ ለመደምሰሱ ምክንያት ሆነ።


ተተኪ አይኑረው፥ በቀጣይ ትውልድ ስማቸው ይደምሰስ።


የቤቱም ንብረት ይሰናበታል፥ በቁጣው ቀን በጐርፍ ተጠራርጎ ይወሰዳል።


“እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞች ሁሉና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ፤ ሥርንና ቅርንጫፍንም አያስቀርላቸውም።


ምድርህን አጥፍተሃልና፥ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘለዓለም የተጠራ አይሆንም።


እሾኽ የሚነካ ሁሉ፥ የብረት መሣሪያ ወይም የጦር ዘንግ ይይዛል፤ እነሱም ባሉበት ስፍራ ፈጽመው በእሳት ይቃጠላሉ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements