Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 16:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፥ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘለዓለም ፍሥሐ አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አሁ​ንም አባ​ረ​ሩኝ፤ ከበ​ቡ​ኝም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደ​ረጉ።

See the chapter Copy




መዝሙር 16:11
28 Cross References  

የሕይወትን መንገድ አስታወቅኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን ትሞላብኛለህ።”


አሁንም ሳትሰናከሉ ሊጠብቃችሁ፥ በክብሩ ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ ሊያቆማችሁ ለሚችለው፤


የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ድረስ እንድትሞሉ፥ እውቀትን የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ ነው።


የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።


እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።


ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ጠባብ፥ መንገዱም ቀጭን ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።


ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።


ቀላል የሆነው ጊዜያዊ መከራችን ከመመዘኛዎች ሁሉ ለሚያልፈው ለዘላለማዊ ክብር ያዘጋጀናል።


ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው፤ በዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን የማውቀው በከፊል ነው፤ በዚያን ጊዜ እኔ ራሴ ሙሉ በሙሉ የታወቅሁትን ያህል ዐውቃለሁ።


በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም።


ጌታ ኢየሱስ ይህን ከተናገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


በጎቹን በቀኙ ፍየሎቹን ደግሞ በግራው ያቆማቸዋል።


በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፥ የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


እነዚህ ወደ ዘለዓለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለም ሕይወት ይሄዳሉ።”


ወደ እርሷ የሚገቡ ሁሉ አይመለሱም፥ ወደ ሕይወት ጎዳናም አይደርሱም፥


የቀና የሕይወትን መንገድ አታገኝም፥ በአካሄድዋ የተቅበዘበዘች ናት፥ የሚታወቅም አይደለም።


“እነሆ፥ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ፤” አለ።


በልቤ ደስታን ጨመርህ፥ ከስንዴ ፍሬያቸውና ከወይናቸው ይልቅ በዛ።


ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም እልል ይበሉ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements