Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 141:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አቤቱ ጌታ፥ ዐይኖቼ ወደ አንተ ናቸውና፥ በአንተ ታመንሁ፥ ነፍሴን አትተዋት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ፤ መጠጊያዬም አንተ ነህ፤ እንግዲህ ነፍሴን አትተዋት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔ ግን በአንተ መተማመኔን አልተውም፤ የአንተንም ጥበቃ ስለምፈልግ እንድሞት አታድርገኝ!

See the chapter Copy




መዝሙር 141:8
9 Cross References  

አምላካችን ሆይ! አንተ አትፈርድባቸውምን? ይህን የመጣብንን ታላቅ ወገን ልንቋቋመው አንችልም፤ ዐይኖቻችን ወደ አንተ ከማንሣት በቀር የምናደርገውን ነገር አናውቅም።”


ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።


“ወላጆች እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፤ ወደ እናንተ እመጣለሁ።


ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።


ተግሣጹን ተቀበሉ ጌታ እንዳይቈጣ እናንተም በመንገድ እንዳትጠፉ፥ ቁጣው ፈጥና ትነድዳለችና። በእርሱ የታመኑ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። በጌታ ታመንሁ፥ ነፍሴን፦ እንዴት እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ሽሺ ትሉአታላችሁ?


Follow us:

Advertisements


Advertisements