Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 126:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ ለኛ ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን፤ እኛም ደስ አለን።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በእርግጥም ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርጎልናል፤ እጅግም ተደስተናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እነሆ፥ ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ናቸው፥ የሆ​ድም ፍሬ የእ​ርሱ ዋጋ ነው።

See the chapter Copy




መዝሙር 126:3
19 Cross References  

ሁሉን የሚችል እርሱ ለእኔ ታላላቅ ነገሮችን አድርጎአልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው።


ታያላችሁ፥ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፥ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የጌታም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፥ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳን፥ ኃይልም፥ መንግሥትም እንዲሁም የክርስቶስ ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።


በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም በጻድቅ ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።


አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።


ማርያምም እንዲህ አለች፦ “ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች፤


በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።


ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፥ በበደል የሚሄድንም የጠጉሩን አናት ይቀጠቅጣል።


የሰሜንንም ሠራዊት ከእናንተ ዘንድ አርቃለሁ፥ ወደ በረሃና ወደ ምድረ በዳ፥ ፊቱን ወደ ምሥራቁ ባሕር ጀርባውንም ወደ ምዕራቡ ባሕር አድርጌ አሳድደዋለሁ፥ እርሱም ብዙ ነገር አድርጎአልና ግማቱ ይወጣል፥ ክርፋቱም ይነሣል አለ።


ምድር ሆይ፥ ጌታ ታላቅ ነገር አድርጎአልና አትፍሪ፥ ደስም ይበልሽ፥ እልልም በዪ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements