Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 102:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጌታ ከመቅደሱ ከፍታ ሆኖ ተመልክቶአልና፥ ከሰማይ ሆኖ ምድርን አይቶአልና፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይኸውም የእስረኞችን ጩኸት ይሰማ ዘንድ፣ ሞት የተፈረደባቸውንም ያድን ዘንድ ነው።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ይህንንም ያደረገው የእስረኞችን መቃተት ሰምቶ ሞት የተፈረደባቸውንም ነጻ ለማውጣት ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ቃሉን የም​ት​ፈ​ጽሙ፥ ብር​ቱ​ዎ​ችና ኀያ​ላን፥ የቃ​ሉ​ንም ድምፅ የም​ት​ሰሙ መላ​እ​ክቱ ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤

See the chapter Copy




መዝሙር 102:20
15 Cross References  

የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፥ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።


ለተበደሉት የሚፈርድ፥ ለተራቡ ምግብን የሚሰጥ ነው። ጌታ የታሰሩትን ይፈታል፥


ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


ዓለሙን ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንም ያፈረሰ፥ ምርኮኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልላከ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።


ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ።


በከተማው ለመሞት የሚያጣጥሩ ያቃስታሉ፥ ቁስለኞችም ለእርዳታ ይጮኻሉ፥ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።”


ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’


Follow us:

Advertisements


Advertisements