Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 102:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 አቤቱ፥ አሕዛብ ስምህን፥ ነገሥታትም ሁሉ ክብርህን ይፈራሉ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ጽዮንን መልሶ ይሠራታልና፤ በክብሩም ይገለጣል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር ጽዮንን እንደገና በሚሠራበት ጊዜ በክብሩ ይገለጣል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነፍሱ ከእ​ርሱ ይወ​ጣ​ልና፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ኖ​ር​ምና ስፍ​ራ​ው​ንም ደግሞ አያ​ው​ቀ​ው​ምና።

See the chapter Copy




መዝሙር 102:16
17 Cross References  

የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልንም ምርኮ እመልሳለሁ፥ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ።


ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።


የሕዝቤን ሴቶች ከተዋበ ቤታቸው አስወጣችኋቸው፤ ከሕፃናቶቻቸውም ክብሬን ለዘለዓለም ወሰዳችሁ።


የእስራኤል ድንግል ሆይ! እንደገና እሠራሻለሁ አንቺም ትሠሪያለሽ፤ እንደገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ሐሤት በሚያደርጉ ዘፋኞች ሽብሸባ እያሸበሸብሽ ትወጫለሽ።


ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቃለሁ፤ አሕዛብንና ልሣናትን ሁሉ የምትሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፤ እነርሱም ይመጣሉ፥ ክብሬንም ያያሉ።


ጌታ ለክብሩ የተከላቸው ጽድቃዊ የባሉጥ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች በአመድ ፋንታ አክሊልን እንዳደርግላቸው፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘን መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እንድሰጣቸው ልኮኛል።


የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።


በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፥ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።”


ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።


ሰማይና ምድር ባሕርም በእርሷም የሚንቀሳቀስ ሁሉ ያመሰግኑታል።


መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር፥ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።


እርሱ የጌታ ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የጌታን ስም፥ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።


አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ፥ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።


“በመንጋው ውስጥ ተባዕት እያለው ለጌታ ተስሎት እያለ ነውር ያለበትን የሚሠዋ ተንኮለኛ ሰው የተረገመ ነው። እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝና፥” ይላል የሠራዊት ጌታ፥ “ስሜም በሕዝቦች መካከል የተፈራ ነውና።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements