Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




መዝሙር 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ክፉ ሰዎች ይታበያሉ፤ ድኾችንም ያሳድዳሉ፤ ለሌሎች በዘረጉት ወጥመድ ራሳቸው ይጠመዱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ኀጢ​አ​ተ​ኞች እነሆ፥ ቀስ​ታ​ቸ​ውን ገት​ረ​ዋ​ልና፥ ፍላ​ጻ​ቸ​ው​ንም በአ​ው​ታር አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋ​ልና፥ ልበ ቅኖ​ቹን በስ​ውር ይነ​ድፉ ዘንድ።

See the chapter Copy




መዝሙር 10:2
18 Cross References  

ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።


ጽኑ ፍቅርህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም ልባቸው በቀና ላይ ዘርጋ።


ጉድጓድን ማሰ ቈፈረም። በሠራውም ጉድጓድ ይወድቃል።


ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


ባርያህን በመልካም ጠብቀው፥ ትዕቢተኞችም አይጋፉኝ።


አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።


አቤቱ፥ ከክፉዎች እጅ ጠብቀኝ፥ እርምጃዬንም ሊያሰናክሉ ከመከሩ ከዓመፀኞች አድነኝ።


ኃጢአተኞች ጉድጓድ ቆፈሩልኝ፥ አቤቱ፥ እንደ ሕግህ ግን አይደለም።


የትዕቢተኞች ዓመጽ በላዬ በዛ፥ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።


የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “ሐሰት ተናግረሃል፤ ጌታ አምላካችን፦ ‘በዚያ ለመቀመጥ ወደ ግብጽ አትግቡ’ ብሎ እንድትናገር አልላከህም፤


የሚያዩህ ይመለከቱሃልና፦ በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥


አንተም በልብህ፦ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤


ደንቦችህን ለመጠበቅ መንገዶቼ ምነው በቀኑ።


በትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር ላይ ጌታ ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አሁን አወቅሁ።”


እንዳትለቅቃቸው አሁንም በሕዝቤ ላይ ትታበያለህ፤


በቸርነት ለመመላለስ አላሰበምና፥ ችግረኛንና ምስኪንን ልቡ የተሰበረውንም ለመግደል ያሳድድ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements