Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፤ ርምጃዎቿም በቀጥታ ወደ ሲኦል ያመራሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 መንገዶችዋ ወደ ሞት የሚያደርሱ ናቸው፤ እርምጃዎችዋም ወደ ሲኦል ይመራሉ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግሮችዋም ወደ ስንፍና ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሞትና ወደ ሲኦል ያደርሳል። ፍለጋዋ ከኀጢአት ቦታ አይርቅም፥

See the chapter Copy




ምሳሌ 5:5
6 Cross References  

ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፥ ወደ ሞት ማደርያዎች የሚወርድ ነው።


አየሁም፤ እነሆም የገረጣ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።


ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ፥ የእናትህንም ትምህርት አትተው፥


ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።


እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements