Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 23:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ቀና ብለህ እያየኸው ይጠፋል፥ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር ለራሱ ክንፍ ያበጃልና።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በሀብት ላይ ዐይንህን ብትጥል፣ ወዲያው ይጠፋል፤ ወደ ሰማይ እንደሚበርር ንስር፣ በርግጥ ክንፍ አውጥቶ ይበርራል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንዲህ ዐይነቱ ሀብት እያየኸው ወዲያው ይጠፋል፤ በሰማይ እንደ ሚበርር ንስር ክንፍ አውጥቶ ይበራል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በእርሱ ላይ ዐይንህን ብታተኩር አታገኘውም፥ ለእርሱ የንስር ክንፍ ተዘጋጅቶለታልና። ወደሚቆምበትም ቤት ይመለሳልና።

See the chapter Copy




ምሳሌ 23:5
17 Cross References  

ሃብት ለዘለዓለም አይኖርምና፥ ዘውድም ለትውልድ ሁሉ አይጸናምና።


ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፥ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን ምኞት፥ በኑሮ ደረጃ መመካት፥ ከዓለም ነው እንጂ ከአብ አይደለም።


በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑትን ሰዎች እንዳይታበዩ በሚያልፍም ባለጠግነት ላይ ሳይሆን እንድንደሰትበት ሁሉን አትረፍርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር ላይ ተስፋ እንዲያደርጉ እዘዛቸው።


“ብልና ዝገት በሚያጠፉት፥ ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁበት በምድር ላይ ሃብት አትሰብስቡ፤


ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።


አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።


ዓይንህና ልብህ ግን ለተጭበረበረ ትርፍ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ነው።”


ሰባኪው፦ ከንቱ፥ ከንቱ፥ የከንቱ ከንቱ፥ ሁሉ ከንቱ ነው ይላል።


እነሆ፥ ዘመኖቼን ከእጅ መዳፍ አሳጠርካቸው፥ አካሌም በፊትህ እንደ ኢምንት ነው። ሰው ሁሉ በእውነት ከንቱ ነው።


እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


ባለ ጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን ለመጨረሻ ጊዜ ነው፥ ዓይኑን ሲከፍት፥ እርሱም የለም።


“ውሰደው፥ በበጎ ተመልከተው፥ የሚሻውንም ነገር አድርግለት እንጂ ምንም ዓይነት ክፉ ነገር አታድርግበት።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements