Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 20:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ሕይወቱ በድቅድቅ ጨለማ ጊዜ እንደሚጠፋ መብራት ይሆናል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አባቱንና እናቱን የሚያማ ብርሃኑ ይጠፋል፥ የዐይኖቹ ብሌንም ጨለማን ያያል።

See the chapter Copy




ምሳሌ 20:20
16 Cross References  

አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።


አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።


ለክፉ ሰው የወደፊት ተስፋ የለውምና፥ የክፉዎች መብራት ይጠፋልና።


የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት’ ብሎ አዞአልና፤


በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።


ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፥ ደሙ በራሱ ላይ ነው።


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


ሞኞቹ ብልሆቹን ‘መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን’ አሉአቸው።


በዚያን ጊዜ ንጉሡ አገልጋዮቹን ‘እጁንና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት፤ በዚያም ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፤’ አለ።


ሁልጊዜ ለጻድቃን ብርሃን ነው፥ የኀጥኣን መብራት ግን ይጠፋል።


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


ከብርሃን ወደ ጨለማ ያፈልሱታል፥ ከዓለምም ያሳድዱታል።


በመጀመሪያ ፈጥኖ የተከማቸ ርስት ፍጻሜው አይባረክም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements