Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 2:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጥበብ ወደ ልብህ ትገባለችና፥ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለችና፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ጥበብ ልብህ ውስጥ ትገባለችና፤ ዕውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ጠቢብ ትሆናለህ፤ ዕውቀትም ደስታን ይሰጥሃል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ጥበብ ወደ ልብህ በመጣች ጊዜ፥ ዕውቀትም ለነፍስህ መልካምና ክብር በሆነች ጊዜ፥

See the chapter Copy




ምሳሌ 2:10
15 Cross References  

ቃላትህ ተገኝተዋል እኔም በልቼአቸዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ጌታ ሆይ! በስምህ ተጠርቻለሁና ቃላትህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑኝ።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥ የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ።


ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።


ቃሌ ለእርሱ ይጣፍጠው፥ እኔም በጌታ ደስ ይለኛል።


ጌታን መፍራት ንጹሕ ነው፥ ለዘለዓለም ይኖራል፥ የጌታ ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ናቸው።


የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።


በአዋቂ ልብ ጥበብ ትቀመጣለች፥ በሰነፎች ውስጥ ግን አትታወቅም።


ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፥ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።


አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።


ብልሃትን ለአላዋቂዎች ለመስጠት ለወጣቶችም እውቀትንና ጥንቃቄን፥


እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ አስደሳች ነገር ይሆንልሃልና።


አትተዋት፥ ትጠብቅሃለች፥ ውደዳት፥ ትንከባከብህማለች።


Follow us:

Advertisements


Advertisements