Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ምሳሌ 18:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ሞኝ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሞኝ በሚናገርበት ጊዜ ራሱን በጒዳት ላይ ይጥላል፤ አነጋገሩም ወጥመድ ሆኖ ይይዘዋል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

See the chapter Copy




ምሳሌ 18:7
16 Cross References  

አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋት ያገኘዋል።


ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።


ጠቢባን እውቀትን ያከማቻሉ፥ የአላዋቂ አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል።


አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።


እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥


በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥ በአፍህ ቃል ከተያዝህ።


በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፥ በከንፈሩ ሞኝ የሆነ ግን ይወድቃል።


ባያትም ጊዜ ልብሱን በመቅደድ፥ “ወይኔ ልጄ ጉድ አደረግሽኝ ጭንቅም ላይ ጣልሺኝ፤ ማስቀረት የማልችለውን ስእለት ለጌታ ተስያለሁና” ብሎ በኀዘን ጮኸ።


የጆሮ ጠቢ ቃል እንደ ጣፋጭ መብል ነው፥ እርሱም እስከ ሆድ ጉርጆች ድረስ ይወርዳል።


ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል።


በሰነፍ አፍ የትዕቢት በትር አለ፥ የጠቢባን ከንፈር ግን ትጠብቃቸዋለች።


ገንዘብ ላደረገው ሰው እውቀት የሕይወት ምንጭ ነው፥ ስንፍና ግን የሰነፎች ቅጣት ነው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements