Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ፊልሞና 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በጸሎቴ እያሰብኩህ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ አምላኬን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በጸሎቴ አንተን እያሰብኩ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4-5 በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4-5 በጌታ በኢየሱስ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለህ ስለ ፍቅርህና ስለ እምነትህ ሰምቼ፥ በጸሎቴ እያሳሰብሁ ሁልጊዜ አምላኬን አመሰግናለሁ፤

See the chapter Copy




ፊልሞና 1:4
8 Cross References  

እምነታችሁ በዓለም ሁሉ ስለ ተሰማ፥ ስለ ሁላችሁም በመጀመሪያ አምላኬን በኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግናለሁ።


ስለ እናንተን በጸሎቴ ባስታወስኩ ቍጥር ምስጋናዬን አላቋረጥኩም።


ያለማቋረጥ ሌሊትና ቀን በጸሎቴ አንተን በማስታወስ፥ አባቶቼ እንዳደረጉት በንጹሕ ኅሊና የማገለግለውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤


ወንድሞች ሆይ! እምነታችሁ እጅግ አድጎአልና፥ የእናንተም የእያንዳንዳችሁ ሁሉ ፍቅር ለእርስ በርሳችሁ በዝቶአልና፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ልናመሰግን ግዴታ አለብን፤


በጸሎታችን ጊዜ ያለማቋረጥ እያነሣናችሁ ስለ ሁላችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ሁልጊዜ እናቀርባለን፤


ስለ እናንተ ስንጸልይ፥ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን ሁልጊዜ እናመሰግናለን፤


እናንተን ባሰብኋችሁ ጊዜ ሁሉ አምላኬን አመሰግነዋለሁ፤


በጌታ በኢየሱስ ዘንድ፤ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለው ፍቅርህና እምነትህ እሰማለሁና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements