ዘኍል 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው ሬሳን በመንካት ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ እንዲህም ሆኖ እንኳ ለጌታ የፋሲካን በዓል ያክብር። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘ከእናንተ ወይም ከዘሮቻችሁ ማንኛውም ሰው በሬሳ ምክንያት ቢረክስ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ማክበር ይችላል፤ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእናንተም ሆነ ከዘራችሁ ሰዎች በድን በመንካት ቢረክሱ ወይም ወደ ሩቅ አገር ለመሄድ በጒዞ ላይ ቢሆኑና የፋሲካን በዓል ለማክበር ቢፈልጉ፥ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ ወይም በተወለዳችሁበት ሀገር ያለም ቢሆን እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ። See the chapter |