ዘኍል 8:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ወንድሙንም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገልግል፤ ሰሞናቸውንም ይጠብቅ። ነገር ግን አገልግሎቱን ይተው። እንዲሁ በየሰሞናቸው ለሌዋውያን ታደርጋለህ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ። See the chapter |