Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 7:86 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

86 ዕጣንም የተሞሉት ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ሙዳዮች፥ እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል ነበሩ፤ የሙዳዮቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

86 ዕጣን የሞላባቸው ዐሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎችም እያንዳንዳቸው በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ሰቅል መዘኑ፤ በአጠቃላይ የወርቅ ጭልፋዎቹ ክብደት አንድ መቶ ሃያ ሰቅል ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

86 ዐሥራ ሁለቱ ከወርቅ የተሠሩት የዕጣን ማስቀመጫዎች በመቅደሱ ሚዛን መሠረት እያንዳንዳቸው ዐሥር ሰቅል የሚመዝኑ ሲሆኑ በጠቅላላው አንድ መቶ ኻያ ሰቅል ይመዝኑ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

86 ዕጣ​ንም የተ​ሞሉ ዐሥራ ሁለት የወ​ርቅ ጭል​ፋ​ዎች፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ በመ​ቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን ዐሥር ዐሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭ​ል​ፋ​ዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሃያ ሰቅል ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

86 ዕጣንም የተሞሉ አሥራ ሁለቱ የወርቅ ጭልፋዎች፥ እያንዳንዱ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን አሥር አሥር ሰቅል ነበረ፤ የጭልፋዎቹ ወርቅ ሁሉ መቶ ሀያ ሰቅል ነበረ።

See the chapter Copy




ዘኍል 7:86
6 Cross References  

ለማፍሰሻም እንዲሆኑ ወጭቶችዋን ጭልፋዎችዋንም መቅጃዎችዋንም ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።


በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።


እያንዳንዱም የብር ወጭት መቶ ሠላሳ ሰቅል፥ እያንዳንዱም ጐድጓዳ ሳሕን ሰባ ሰቅል ነበረ፤ የዚህም ዕቃ ሁሉ ብር በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰቅል ነበረ።


የሚቃጠለው መሥዋዕት ከብት ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖች፥ ዐሥራ ሁለትም አውራ በጎች፥ ዐሥራ ሁለትም የአንድ ዓመት ተባት ጠቦቶች ከእህሉ ቁርባን ጋር ነበሩ፤ የኃጢአትም መሥዋዕት አውራ ፍየሎች ዐሥራ ሁለት ነበሩ።


ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።


ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements