ዘኍል 6:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 “ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ የመግዛት አቅሙ ከሚፈቅድለት ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለጌታ የሚያቀርበው የቁርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 “ ‘ስእለቱን ለመፈጸም ለእግዚአብሔር ለሚሳል ናዝራዊ ሕጉ ይኸው ነው፤ ሊቀርብ ከሚችለው በላይ ለእግዚአብሔር ለመስጠት ቃል ለሚገባው ነገር እንደ ናዝራዊነቱ በተሳለው መሠረት መሆን አለበት። በናዝራዊነት ሕግ መሠረት የተሳለውን ስእለት መፈጸም ይገባዋል።’ ” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 “እንግዲህ እነዚህ ስለ ናዝራውያን የተሰጡ የሕግ መመሪያዎች ናቸው፤ ነገር ግን አንድ ናዝራዊ በስእለቱ መሠረት ሊያቀርብ ከሚገባው በላይ ለመስጠት ቃል ቢገባ በገባው ቃል መሠረት ስእለቱን መፈጸም አለበት።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 “ስእለቱን የተሳለው የባለስእለቱ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ስእለቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ስእለቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ እጁም ከሚያገኘው ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የቍርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል። See the chapter |