Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ቁርባኑንም ለጌታ ያቅርብ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለበትን አውራ በግ ለአንድነት መሥዋዕት፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እዚያም መሥዋዕቱን ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ ይኸውም፣ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባዕት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኀጢአት መሥዋዕት እንዲሁም እንከን የሌለበት አውራ በግ ለኅብረት መሥዋዕት ሲሆን፣

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እዚያ ቊርባኑን ለእግዚአብሔር ያቀርባል፤ ይኸውም ለሚቃጠል መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላው የበግ ጠቦት፥ ስለ ኃጢአት ስርየት ለሚቀርበውም መሥዋዕት አንድ ዓመት የሞላት አንዲት የበግ ቄብ እንዲሁም የአንድነት መሥዋዕት አንድ አውራ በግ ያቀርባል ማለት ነው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነውር የሌ​ለ​በት የአ​ንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ትን የአ​ንድ ዓመት እን​ስት ጠቦት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አውራ በግ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ቍርባኑንም ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለበትን አውራ በግ ለደኅንነት መሥዋዕት፥

See the chapter Copy




ዘኍል 6:14
12 Cross References  

“ስለ ኃጢአትም መሥዋዕት የበግ ጠቦት ቢያቀርብ፥ ነውር የሌለባትን እንስት ያመጣል።


“ለጌታም ለአንድነት መሥዋዕት የሚያቀርበው ቁርባኑ ከበጎች ተባት ወይም እንስት ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ያቀርባል።


ነገር ግን ነውርና እድፍ እንደሌለው በግ ደም፥ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው፥


የጌታንም ቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙትን ሌዋውያንን እግዚአብሔር ስለረዳቸው ሰባት በሬዎችና ሰባት አውራ በጎች ሰዉ።


“አንድ ሰው ባለማወቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ለኃጢአት መሥዋዕት አንዲት የአንድ ዓመት እንስት ፍየል ያቀርባል።


“በስምንተኛውም ቀን ነውር የሌለባቸውን ሁለት ተባት ጠቦት፥ ነውር የሌለባትንም አንዲት የዓመት እንስት ጠቦት፥ ለእህሉም ቁርባን ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ የሆነ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት፥ ዘይትም ያለበትን አንድ የሎግ መስፈሪያ ይወስዳል።


“ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ባለማወቅ ጌታ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዱን ተላልፎ ኃጢአት ቢሠራና ቢበድል፥


ከወጠጤዎች መዓዛ ጋር ለሚቃጠል መሥዋዕት ፍሪዳን አቀርባለሁ፥ ላሞችንና ፍየሎችን እሠዋልሃለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements