Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶቹንም፥ እግሮቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ መገልገያውንም ሁሉ፥

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ሜራሪያውያንም የማደሪያውን ድንኳን ሳንቃዎች፣ መወርወሪያዎች፣ ምሰሶዎች፣ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን እግሮች፣ የማደሪያ ዕቃዎችን ሁሉና ከነዚሁ ጋራ ተያይዞ አገልግሎት የሚሰጠውን ሁሉ ለመጠበቅ ተሹመው ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 የእነርሱም ኀላፊነት በድንኳኑ ተራዳዎችና በመወርወሪያዎቻቸው፥ በምሰሶቹና ምሰሶቹ በሚቆሙባቸው እግሮች፥ እንዲሁም በሌሎች የመገልገያ ዕቃዎች ላይ ሲሆን፥ በአጠቃላይ እነዚህን ነገሮች በሚመለከት ሥራ ኀላፊነቱ የእነርሱ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 የሜ​ራ​ሪም ልጆች የሚ​ጠ​ብ​ቁት የድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኩላ​ቦች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ችም፥ እግ​ሮ​ቹም፥

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያው ሳንቆች፥ መወርወሪያዎችም፥ ተራዳዎችም፥ እግሮቹም፥ ዕቃውም ሁሉ፥

See the chapter Copy




ዘኍል 3:36
14 Cross References  

ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶች ከግራር እንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም እግሮች አድርግላቸው።”


በወርቅ በተለበጡት ከግራር እንጨትም በተሠሩት በአራቱ ምሰሶች ላይ ስቀለው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ፥ አራቱም እግሮቻቸው ከብር የተሠሩ ይሁኑ።


በካህኑም በአሮን ልጅ በኢታምር ቁጥጥ ሥር ሆነው ለሜራሪ ልጆች እንደ አገልግሎታቸው አራት ሰረገሎችንና ስምንት በሬዎችን ሰጣቸው።


ማደሪያውን ወደ ሙሴ አመጡት፥ ድንኳኑን፥ የመገልገያ ዕቃዎቹን ሁሉ፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቆቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶቹንና እግሮቹን፥


አራት ምሰሶዎችን ከግራር እንጨት ሠርቶ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኩላቦቻቸው የወርቅ ነበሩ፤ ለእነርሱም አራት የብር እግሮች ሠራላቸው።


የማደሪያውን ካስማዎች፥ የአደባባዩን ካስማዎችና አውታሮቻቸውን፤


ማደሪያውን፥ ድንኳኑን፥ መደረቢያውን፥ መያዣዎቹን፥ ሳንቃዎቹን፥ መወርወሪያዎቹን፥ ምሰሶዎቹን፥ እግሮቹን፤


የሜራሪም ወገኖች አባቶች ቤት አለቃ የአቢካኢል ልጅ ሱሪኤል ነበረ፤ እነርሱም በማደሪያው አጠገብ በሰሜን በኩል ይሰፍራሉ።


በዙሪያውም የሚቆሙትን የአደባባይ ምሰሶች፥ እግሮቹንም፥ ካስማዎቹንም፥ አውታሮቹንም ይሆናል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements