ዘኍል 3:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም የመቅደሱን ግዴታ በሚፈጽሙት ላይ ተቆጣጣሪ ይሆናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ዋናው የሌዋውያን አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነው፤ እርሱም መቅደሱን ለመጠበቅ ኀላፊ በሆኑት ላይ ተሹሞ ነበር። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 የሌዋውያን ሁሉ አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነበር፤ እርሱ በተቀደሰው ስፍራ ለሚያገለግሉት ሰዎች ሁሉ የበላይ ኀላፊ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የተቀደሱ ነገሮችን ይጠብቅ ዘንድ የተሾመው የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 የሌዋውያንም አለቆች አለቃ የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር ይሆናል፤ እርሱም መቅደሱን በሚጠብቁት ላይ ይሆናል። See the chapter |