Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 3:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በጌድሶን ውስጥ የሎቤናውያን ወገንና የሰሜአውያን ወገን ይካተቱ ነበር፤ የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሊብናና የሰሜኢ ጐሣዎች ከጌርሶን ወገን ናቸው፤ እነዚህ የጌርሶን ጐሣዎች ነበሩ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የሊብኒና የሺምዒ ቤተሰቦች በጌርሾን ጐሣ ውስጥ ተጠቃለው ነበር፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ለጌ​ድ​ሶን የሎ​ቤን ወገን፥ የሰ​ሜ​ይም ወገን ነበ​ሩት፤ የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ለጌድሶን የሎቤናውያን ወገን የሰሜአውያንም ወገን ነበሩት፤ የጌድሶናውያን ወገኖች እነዚህ ናቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 3:21
9 Cross References  

የሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው፤ ሞሖሊ፥ ሙሲ። የሌዋውያን ወገኖች በየአባቶቻቸው ቤቶች እነዚህ ናቸው።


ከእነርሱ የተቈጠሩት ዕድሜው አንድ ወር የሞላውና ከዚያም በላይ ያለው የወንዶች ሁሉ ቍጥር ሰባት ሺህ አምስት መቶ ነበረ።


እነዚህ የሌዊ ወገኖች ናቸው፤ የሊብናውያን ወገን፥ የኬብሮናውያን ወገን፥ የሞሖላውያን ወገን፥ የሙሳውያን ወገን፥ የቆሬያውያን ወገን። ቀዓትም እንበረምን ወለደ።


እነዚህ የሌዊ ልጆች ስሞች እንደ ትውልዳቸው ጌርሾን፥ ቀሃት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


የጌድሶንም ልጆች ስሞች በየወገኖቻቸው እነዚህ ናቸው፤ ሎቤኒ፥ ሰሜኢ።


“እንዲሁም የጌድሶንን ልጆች በየአባቶቻቸው ቤቶች በየወገኖቻቸውም የሕዝብ ቈጠራ አድርግ።


ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።


እነዚህም የጌድሶን ልጆች ስሞች ናቸው፤ ሎቤኒ እና ሰሜኢ።


የሌዊ ቤት ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥ የሰሜኢ ወገን ለብቻው፥ ሴቶቻቸውም ለብቻቸው፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements