ዘኍል 29:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን ከመጠጡም ቁርባናቸው ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ አውራ ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ከመደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቊርባን ሌላ በተጨማሪ ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ለኀጢአትም መሥዋዕት ከፍየሎች አንድ አውራ ፍየልን ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን፥ ከመጠጡም ቍርባናቸው ሌላ የሚቀርቡ ናቸው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየልን ታቀርባላችሁ፤ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባናቸው ሌላ የሚቀርቡ ናቸው። See the chapter |