ዘኍል 28:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 “ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቁርባን ለጌታ ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ የጉልበት ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 “ ‘በሱባዔ በሚደረገው የመከር በዓል፣ አዲስ የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር በምታቀርቡበት በፍሬ በኵራት ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ የዘወትር ተግባርም አትሥሩበት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 “በመከር በዓል መጀመሪያ ቀን አዲስ እህል ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ በምታቀርቡበት ጊዜ ለአምልኮ ትሰበሰባላችሁ፤ ሥራም አትሠሩም፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 “በበዓለ ሠዊት ቀን በሰንበታት በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ቀን ይሆንላችኋል፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ደግሞ በበኵራት ቀን ከሰባቱ ሱባዔ በዓላችሁ አዲሱን የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ባቀረባችሁ ጊዜ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሆንላችኋል፤ የተግባርን ሥራ ሁሉ አትሥሩበት። See the chapter |