ዘኍል 28:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ “‘ማዕዴን፥ ለእኔ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርበውን ቁርባኔን፥ መባዬን በተገቢው ጊዜ እንድታቀርቡልኝ በጥንቃቄ ልብ በሉ።’ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ስጣቸው፤ ‘ሽታው ደስ እንዲያሠኘኝ በእሳት የሚቀርብልኝን የምግብ ቍርባን የተወሰነውን ጊዜ ጠብቃችሁ አቅርቡልኝ።’ See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “ለእስራኤል ሕዝብ የምትሰጣቸው ትእዛዝ ይህ ነው፦ መዓዛው ደስ የሚያሰኝ በእሳት የሚቃጠል የምግብ ቊርባን እንዲያቀርቡልኝ ንገራቸው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ ቍርባኔን፥ መባዬንና የበጎ መዓዛ መሥዋዕቴን በበዓላት ቀኖች ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ መብሌን፥ ለእኔ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በእሳት የተደረገውን ቍርባኔን፥ መባዬን በየጊዜው ታቀርቡልኝ ዘንድ ጠብቁ። See the chapter |