ዘኍል 26:62 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)62 ዕድሜአቸው አንድ ወር የሞላቸውና ከዚያም በላይ ያሉት ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም62 አንድ ወርና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሌዋውያን ወንዶች ሁሉ ተቈጥረው ሃያ ሦስት ሺሕ ሆኑ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋራ ርስት ተካፋዮች ስላልነበሩ ዐብረዋቸው አልተቈጠሩም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም62 ዕድሜአቸው አንድ ወርና ከዚያም በላይ የሆነ የወንዶች ሌዋውያን ጠቅላላ ቊጥር ኻያ ሦስት ሺህ ሆነ፤ እነርሱም ከሌሎቹ እስራኤላውያን ተለይተው ተመዘገቡ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት በእስራኤል ምድር ምንም ዐይነት የርስት ድርሻ ስላልተሰጣቸው ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)62 ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሃያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)62 ከአንድ ወርም ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉ ወንዶች ሁሉ ከእነርሱ የተቈጠሩ ሀያ ሦስት ሺህ ነበሩ። ከእስራኤልም ልጆች መካከል ርስት አልተሰጣቸውምና ከእስራኤል ልጆች ጋር አልተቈጠሩም። See the chapter |