ዘኍል 24:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤልም በትረ መንግሥት ይነሣል፥ የሞዓብንም ግንባር ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 “አየዋለሁ፤ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ በቅርቡ ግን አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል፤ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይነሣል። የሞዓብን ግንባሮች፣ የሤትንም ወንዶች ልጆች ራስ ቅል ያደቅቃል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 አየዋለሁ፤ ነገር ግን አሁን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፤ ግን በቅርብ አይደለም፤ ኮከብ ከያዕቆብ፥ በትረ መንግሥት ከእስራኤል ይወጣል። የሞአብን ድንበር፥ የሴትንም ዘሮች ሁሉ ይደመስሳል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እባርከዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፤ ከእስራኤልም ሰው ይነሣል፥ የሞዓብንም አለቆች ይመታል፤ የሤትንም ልጆች ሁሉ ይማርካል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል። See the chapter |