ዘኍል 22:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ባላቅም ዳግመኛ ከፊተኞቹ ይልቅ እጅግ የበዙና የከበሩ ሌሎችን ሹማምንት ላከ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ከዚያም ባላቅ ከፊተኞቹ ይልቅ ቍጥራቸው የበዛና ይበልጥ የተከበሩ ሌሎች አለቆች ላከ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ከዚያን በኋላ ባላቅ ከፊተኞቹ መልእክተኞች ይበልጥ የተከበሩና ቊጥራቸውም የበዛ ሹማምንት ወደ በለዓም ላከ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ባላቅም ደግሞ ከእነዚያ የበዙና የከበሩ ሌሎችን አለቆች ሰደደ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ባላቅም ደግሞ ከፊተኞች የበዙና የከበሩ ሌሎችን አለቆች ሰደደ። See the chapter |