ዘኍል 21:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እባብን ሠርተህ በእንጨት ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያየው በሕይወት ይኖራል።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እባብ ሠርተህ በዕንጨት ላይ ስቀለው፤ የተነደፈውም ሁሉ ወደ እርሱ በማየት ይድናል” አለው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን “አንድ የነሐስ እባብ ሠርተህ በረዥም ትክል እንጨት ላይ ስቀለው፤ በእባብ የተነከሰ ሁሉ እርሱን በሚያይበት ጊዜ ይድናል” አለው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የናስ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ እባቡም ሰውን ቢነድፍ የተነደፈው ሁሉ ይመልከተው፤ ይድናልም” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው። See the chapter |