Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 21:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ለእርሱም አንድ ሰው በሕይወት እንዳይተርፍ አድርገው እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ ገደሉ፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ስለዚህም እስራኤላውያን ዐግን ከልጆቹና ከመላው ሰራዊቱ ጋራ አንድም ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፏቸው፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ስለዚህ እስራኤላውያን ዖግን፥ ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ፈጅተው ምድሩን ወረሱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 እር​ሱ​ንና ልጆ​ቹን፥ ሕዝ​ቡን ሁሉ አንድ ሰው ሳያ​መ​ልጥ መቱ፤ ምድ​ሩ​ንም ወረሱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 እርሱንና ልጆቹን ሕዝቡንም ሁሉ መቱ ሰውም አልቀረለትም፤ ምድሩንም ወረሱ።

See the chapter Copy




ዘኍል 21:35
13 Cross References  

በባሳን የነበረውን በአስታሮትና በኤድራይ የነገሠውን የዐግን መንግሥት ሁሉ፤ እርሱም ብቻ ከራፋይም የቀረ ነበረ፤ እነዚህንም ሙሴ ድል አድርጎ አስወጣቸው።


በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ተቀምጠው ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን ነጠቁአቸው፥ ጌታ የሰጣቸውን እስራኤላውያን በርስት ምድራቸው እንዳደረጉት፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ተቀመጡ።


ጌታ የእስራኤል ማኅበር እንዲወርሰው ያደረገው ምድር ሲሆን፥ ለእንስሶች የተመቸ ምድር ነው፤ ለእኛም ለባርያዎችህ እንስሶች አሉን።”


ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ከወጡ በኋላ ድል በነሱት፥ በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፥ በቤተፌዖር አንጻር ባለው ሸለቆ በዮርዳኖስ ማዶ ያወጃቸው።


እነርሱም የእርሱን ምድርና እንዲሁም በዮርዳኖስ ምሥራቅ የምትገኘውን ባሳንን ይገዛ የነበረውን የሌላውን አሞራዊ ንጉሥ የዖግን ምድር ወረሱ።


ጌታ የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል።


ጌታም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ግብፃውያን፥ አሞራውያን፥ አሞናውያን፥ ፍልስጥኤማውያን፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements