Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል መምጣቱን ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ጦርነት አደረገ ከእርሱም ምርኮ ማረከ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ እስራኤል በአታሪም መንገድ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በእስራኤላውያን ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በአ​ዜብ በኩል ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የአ​ራድ ንጉሥ በአ​ታ​ሪን መን​ገድ እስ​ራ​ኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ሰልፍ አደ​ረገ ከእ​ነ​ር​ሱም ምርኮ ማረከ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ።

See the chapter Copy




ዘኍል 21:1
10 Cross References  

የቄናዊው የሙሴ አማት ዘሮች ከይሁዳ ሰዎች ጋር በመሆን ከዘንባባዋ ከተማ ተነሥተው፥ ዓራድ አጠገብ በኔጌብ ውስጥ በይሁዳ ምድረ በዳ ካሉት ሕዝቦች ጋር አብረው ሄዱ፥ እዚያም ከሕዝቡ ጋር ተቀመጡ።


በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደመጡ ሰማ።


የሔርማ ንጉሥ፥ የዓድራ ንጉሥ፥


የጋይም ሰዎች ከእነርሱ ሠላሳ ስድስት ያህል ሰዎችን ገደሉ፤ ከበሩ እስከ ሸባሪም ድረስ አባረሩአቸው በቁልቁለቱም ላይ ሳሉ መቱአቸው፤ የሕዝቡም ልብ ቀለጠ፥ እንደ ውኃም ሆነ።


ሴዎንም፥ እሱና ሕዝቡም ሁሉ፥ ሊጋጠሙን ወደ ያሐጽ ወጡ።


በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ አማሌቃውያንና ከነዓናውያን ወረዱ፥ አሸንፈወዋቸውም እስከ ሔርማ ድረስ አሳደዱአቸው።


አብራምም ከዚያ ተነሣ፥ እየተጓዘም ወደ አዜብ ሄደ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements