Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፥ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጉድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ግዛትህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ በምድርህ አልፈን እንድንሄድ እባክህ ፍቀድልን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን ከመንገድ ውጪ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም አንጠጣም፤ ግዛትህን እስክናልፍ ድረስ ከዋናው መንገድ አንወጣም።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እባ​ክህ፥ በም​ድ​ርህ ላይ እን​ለፍ፤ ወደ እር​ሻም ወደ ወይ​ንም አን​ገ​ባም፤ ከጕ​ድ​ጓ​ዶ​ችም ውኃን አን​ጠ​ጣም፤ በን​ጉሡ ጎዳና እን​ሄ​ዳ​ለን፤ ዳር​ቻ​ህ​ንም እስ​ክ​ና​ልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አን​ልም።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እባክህ፥ በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻም ወደ ወይንም አንገባም፥ ከጕድጓዶችም ውኃን አንጠጣም፤ በንጉሡ ጐዳና እንሄዳለን፥ ዳርቻህንም እስክናልፍ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:17
7 Cross References  

‘በአገርህ ላይ ልለፍ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳልል አውራ ጎዳናውን ይዤ እሄዳለሁ።


ጌታ አምላካችን ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ፥ በሴይር የተቀመጡ የዔሳው ልጆች በዔርም የተቀመጡ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ፥ አድርግልኝ።’”


በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል መምጣቱን ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ጦርነት አደረገ ከእርሱም ምርኮ ማረከ።


እንግዲህ አሁን፥ እነሆ፥ እስራኤል ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እንዳይወርሯቸው ያልፈቀድህላቸው፥ ነገር ግን ትተዋቸው ያላጠፉአቸው፥ የአሞንና የሞዓብ ልጆች የሴይርም ተራራ ሰዎች፥


የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፤ የምጠጣውንም ውሃ በገንዘብ ስጠኝ፤ በእግሬ እንዳልፍ ብቻ ፍድልኝ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements