Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 20:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ ጌታም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ልኮ ከግብጽ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኛም ይረዳን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እርሱም ጩኸታችንን ሰምቶ ከግብጽ የሚያወጣንን መልአክ ላከልን፤ እነሆ አሁን እኛ በግዛትህ ወሰን ላይ ባለችው በቃዴስ እንገኛለን።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድም​ፃ​ች​ንን ሰማ፤ መል​አ​ክ​ንም ልኮ ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ እነ​ሆም፥ በም​ድ​ርህ ዳርቻ ባለ​ችው ከተማ በቃ​ዴስ ተቀ​ም​ጠ​ናል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ እግዚአብሔርም በጮኽን ጊዜ ድምፃችንን ሰማ፥ መልአክንም ሰድዶ ከግብፅ አወጣን፤ እነሆም፥ በምድርህ ዳርቻ ባለችው ከተማ በቃዴስ ተቀምጠናል።

See the chapter Copy




ዘኍል 20:16
14 Cross References  

በእስራኤልም ሠፈር ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ከኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፈቀቅ ብሎ ከኋላቸው ሄደ፤


በፊትህ መልአክ እልካለሁ፥ ከነዓናዊውን፥ አሞራዊውን፥ ኬጢያዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣልሃለሁ።


“በመንገድ እንዲጠብቅህ፥ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ እንዲያስገባህ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እልካለሁ።


ፈርዖንም በቀረበ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ዓይናቸውን አነሡ፥ እነሆም ግብፃውያን ከኋላቸው እየመጡ ነበር፤ የእስራኤልም ልጆች እጅግ ፈሩ፥ ወደ ጌታም ጮኹ።


ደግሞም እኔ ግብፃውያን እንዲሰሩ የሚያስገድዷቸውን የእስራኤልን ልጆች ጩኸት ሰማሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አሰብሁ።


አባቶቻችን ወደ ግብጽ ወረዱ፥ በግብጽም እጅግ ዘመን ተቀመጥን ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ፤


“በምድርህ ላይ ልለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጉድጓድም ውኃን አንጠጣም፤ ግዛትህን አልፈን እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን።”


ከቃዴስም ተጉዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ።


የይሁዳም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገናቸው እስከ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ እስከ ኤዶምያስ ዳርቻ ድረስ ይደርሳል።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


አባቶቻችሁን ወድዶአልና ከእነርሱ በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከእናንተ ጋር ሆኖ በታላቅ ኃይሉ ከግብጽ አወጣችሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements