ዘኍል 19:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን በውኃ ያነጻል፥ በዚህም ንጹሕ ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያነጻ ንጹሕ አይሆንም። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በሦስተኛውና በሰባተኛውም ቀን ሁለመናውን በውሃው ያንጻ፤ ንጹሕም ይሆናል። በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ካላነጻ ግን ንጹሕ አይሆንም። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ለማንጻት በተመደበው ውሃ ራሱን ያነጻል፤ ከዚያም በኋላ ንጹሕ ይሆናል፤ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ራሱን የማያነጻ ከሆነ ሊነጻ አይችልም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እንደዚሁ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያነጻል፤ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያነጻ ንጹሕ አይሆንም። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በዚህም ውኃ በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ያጠራል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ነገር ግን በሦስተኛውና በሰባተኛው ቀን ሁለመናውን ባያጠራ ንጹሕ አይሆንም። See the chapter |