Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ግዴታዎች ይፈጽሙ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱም የመገናኛውን ድንኳን ለመከባከብ ማለትም በድንኳኑ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ሁሉ ኀላፊነት በመውሰድ ዐብረዋችሁ ይሁኑ፤ ከዚህ በተረፈ ግን እናንተ ወዳላችሁበት ማንም ሰው አይጠጋ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱ ዘወትር ከእናንተ ጋር መሥራትና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ስለ ተሰጣቸው አገልግሎት ሁሉ ኀላፊነታቸውን መፈጸም አለባቸው፤ ነገር ግን ሌዋዊ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለመሥራት ወደ እናንተ መቅረብ የለበትም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ከእ​ና​ንተ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይሁኑ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሕግ ይጠ​ብቁ፤ ከባ​ዕድ ወገን የሆነ ሰው ወደ አንተ አይ​ቅ​ረብ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ከእናንተ ጋር በአንድነት ይሁኑ፥ ለድንኳኑም አገልግሎት ሁሉ የመገናኛውን ድንኳን ይጠብቁ፤ ሌላም ሰው ወደ እናንተ አይቅረብ።

See the chapter Copy




ዘኍል 18:4
10 Cross References  

ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።


አሮንንና ልጆቹን ሹማቸው፥ ክህነታቸውንም ይጠብቁ፤ ማናቸውም ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።”


ማደሪያውም ሲነሣ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያውም በሚተከል ጊዜ ሌዋውያን ይትከሉት፤ ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።


እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሁሉ አገልግሎት ግዴታ ይፈጽሙ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።


በጭራሽ ዳግመኛ በእስራኤል ልጆች ላይ ቁጣ እንዳይሆንባቸው እናንተ ራሳችሁ የመቅደሱንና የመሠዊያውን ግዴታዎች ፈጽሙ።


ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ ከሰዎች ከበሬዎችም ከአህዮችም ከበጎችም ከከብቶችም ሁሉ ከኀምሳ አንድ ትወስዳለህ፥ የጌታንም ማደሪያ አገልግሎት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”


ሆኖም ለአገልግሎቱ ሁሉና በእርሱ ውስጥ ለሚደረገው ሁሉ የቤቱን ሥርዓት ጠባቂዎች አደርጋቸዋለሁ።


ነገር ግን በእስራኤል ልጆች ጉባኤ ላይ ቁጣ እንዳይወርድ ሌዋውያን በምስክሩ ማደሪያ ዙሪያ ይስፈሩ፤ ሌዋውያንም የምስክሩን ማደሪያ ይጠብቁ።”


ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements