ዘኍል 18:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የእስራኤል ልጆች እንደ ስጦታ ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለጌታ ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘለዓለም ሰጥቼሃለሁ፤ በጌታ ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ ለዘለዓለም የጨው ቃል ኪዳን ነው።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ከተቀደሰ ቍርባን የሚለየው ሁሉ ለአንተ፣ ለወንድና ለሴት ልጆችህ መደበኛ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም በእግዚአብሔር ፊት ለአንተና ለዘሮችህ ዘላለማዊ የጨው ኪዳን ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 “እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡአቸውን ልዩ ስጦታዎች ሁሉ ለእናንተ፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻችሁ ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ፤ ይህም ከእናንተና ከዘሮቻችሁ ሁሉ ጋር የምገባው የማይሻር የጨው ቃል ኪዳን ነው።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር የሚለዩትን የተቀደሰውን መባ ሁሉ ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ሰጥቼሃለሁ፤ ይህም ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም ሕግና የሁልጊዜ ቃል ኪዳን ነው።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የእስራኤል ልጆች ከተቀደሰው ነገር ሁሉ አንሥተው ለእግዚአብሔር ያቀረቡትን ለአንተ ከአንተም ጋር ለወንዶችና ለሴቶች ልጆችህ ድርሻ እንዲሆን ለዘላለም ሰጥቼሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ፊት ለአንተ ከአንተም ጋር ለዘርህ የጨው ቃል ኪዳን ለዘላለም ነው። See the chapter |