ዘኍል 18:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ማሕፀን የሚከፍትና ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሰውም ሆነ እንስሳ የአንተ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅና ንጹሕ ካልሆነ እንስሳ በኵር ሆኖ የተወለደውን ተባዕት ሁሉ ዋጀው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 “እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡት የሰውም ሆነ የእንስሳ በኲር ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን የበኲር ልጅ ለመዋጀት ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል አለባችሁ፤ እንዲሁም ንጹሕ ስላልሆነው የእንስሳ በኲር ምትክ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል ትችላላችሁ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ ማኅፀን የሚከፍት ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትቤዠዋለህ። See the chapter |