Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 15:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ እንዲያደርጉ፥ በዘርፉም ጫፍ ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል እንዲያኖሩበት እዘዛቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ በየልብሳችሁ ጫፍ ላይ ዘርፍ አድርጉ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በልብሶቻችሁ ጫፍ ላይ ሁሉ ዘርፍ አብጁ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ከሰማያዊ ፈትል የተሠራ ጥለት ይኑረው፤ ይህንንም ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ አድርጉ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ እነ​ር​ሱም በት​ው​ል​ዳ​ቸው ሁሉ በል​ብ​ሳ​ቸው ጫፍ ዘርፍ ያደ​ርጉ ዘንድ፥ በዘ​ር​ፉም ሁሉ ላይ ሰማ​ያዊ ፈትል ያደ​ርጉ ዘንድ እዘ​ዛ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው።

See the chapter Copy




ዘኍል 15:38
5 Cross References  

ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት ሰው እንዲያይላቸው ነው፤ ስለዚህ አሽንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፤


“በምትለብሰው በልብስህ በአራቱ ማዕዘን ዘርፍ አድርግ።


ከበስተኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤ ወዲያውም ደምዋ መፍሰሱን አቆመ።


እነሆ ለዐሥራ ሁለት ዓመታት ደም የሚፈስሳት ሴት ከኋላው ተጠግታ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፤


ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦


Follow us:

Advertisements


Advertisements